(በስደት የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር አባላት አስተባባሪ ኮሚቴ) – በ1966 ዓ.ም ከአውሮፓና ከአሜሪካ የተወጣጡ የዲያስፖራ ፖለቲካኞች ደርግ አብዮተኛ ነው፤ ሂሳዊ ድጋፍ በመስጠት አብረን መስራት እንችላለን በማለት ከፋሺታዊ ደርግ ጋር በማበር ሕዝባዊ አመጹ እንዲኮላሽ ከፍተኛ ድርሻ እንዳበረከቱ የትናንት ትውስታ ነው። በተመሳስሳይ ታሪክ ራሱን ይደግማል እንዲሉ ዛሬም በመግለጫ ጋጋታ የታጠሩ የዲያስፖራ ፖለቲካኞች ቀደም ብለው ከወያኔ ጋር አብረው ይሠሩ ከነበሩ ግለሰቦች ጋር በመሆን በባዕዳን ኃይሎች አስተባባሪነት ወያኔን ያካተተ የሽግግር መንግስት ለመመስረት ደፋ ቀና እያሉ ነው። ይህ አካሄድ በአሁኑ ወቅት እየተቀጣጠለ ያለውን ሕዝባዊ አመፅ ለማኮላሸትና ወያኔ ነፍስ እንዲዘራ ለማድረግ ነው። እየተቀጣጠለ ያለው ሕዝባዊ አመጽ ከዳር እንዲደርስ በስደት የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር አባላት አስተባባሪ ኮሚቴ ድጋፉን ይሰጣል፤የበኩሉንም አስተዋጽኦ ያዳርጋል።
መምህራን በ1966 ዓ.ም ያካሄዱትን አገር አቀፍ የስራ ማቆም አድማ በመጪው 2009 ዓም እንዲደግሙት ማህበሩ ጥሪ ያቀርባል። እየተቀጣጠለ ያለውን ሕዝባዊ አመጽ መምህራን ከተማሪዎቻቸው ጋር በመሆን በስልት ሕዝቡን በማደራጃትና በመቀስቀስ ታሪካዊ ግዴታቸውን እንዲወጡ ያሳስባል። በአጠቃላይ ተማሪዎች፣ ወላጆች፣ ሌሎች የሕብረተሰብ ክፍሎች ትውልድ ገዳይ የትምህርት ፖሊሲ ቀርጾ በትምህርቱ ዘርፍ ላይ ከፍተኛ ወንጀል በመፈጸም ላይ የሚገኛው የወያኔ አገዛዝ በሕዝብ ላይ ጦርነት አውጇልና አገርና ሕዝብን ለማዳን በጋራ የጋራ ጠላታችሁ በሆነው ወያኔ ላይ እንዲትነሱ በስደት የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር አባላት አስተባባሪ ኮሚቴ በድጋሚ ጥሪ ያቀርባል። ሙሉውን መግለጫ ያንብቡ …