የመስከረም 9 ቀን 2009 ዓ.ም.ዜና (19 September, 2016.) – በጎጃምና በጎንደር የቤት ውስጥ አድማው ቀጥሏል፤ ምንጃር ውስጥ ውጥረት አለ – የበአዴን አባላት ርስ በርስ እየተካሰሱ ነው – የወያኔ ባለስልጣኖች በኮንሶ ሕዝብ ላይ እያካሄዱት ያሉት ጭፍጨፋ አልቆመም – በአሜሪካ ዋና ከተማ በዋሽንግተን ደማቅ ትዕየንተ ሕዝብ ተደረገ፤ በሎስ አንጅለስ ቆንስሉ ተያዘ፣ በእየሩሳሌም የተቃውሞ ሰልፍ ተደረገ – የአባይን ጉዳይ አስመልክት የወያኔ፤ የግብጽና የሱዳን ባለስልጣኖች የግድቡን ሁኔታና የሚያስከትለው ችግር ከሚያጠኑ ተቋሞች ጋር ተፈራረሙ – አልሸባብ በደፈጣ የወያኔ ወታደሮችን አጠቃሁ አለ።
ዝርዝር ዜና
በጎንደርና በጎጃም ትናንትና ለሶስተኛ ጊዜ የተጀመረው የቤት ውስጥ አድማ ዛሬም ተጠናክሮ የቀጠለ መሆኑን ከአካባቢዎቹ የሚመጡት ዘገባዎች ይገልጻሉ። በደብረማርቆስ የዩኒቨርስቲ መምህራን ለውይይት በተዘጋጀላቸው መድረክ ላይ ለወያኔ አገዛዝ ያላቸውን ተቃውሞ ገልጸው ስብሰባውን የበተኑት መሆናችው ተነግሯል። ምንጃር ውስጥ ውጥረት መኖሩ የተሰማ ሲሆን በዛት ያለው ወታደር እና ወታደራዊ መኪኖች ወደ አካባቢው መግባታቸው ታውቋል።
በሌላ በኩል በባህር ዳር የባዕዴን አባላት እርስ በርስ መካሰስና መተራመስ የጀመሩ መሆናቸው እየተነገረ ከመሆኑም በላይ በቅርቡ አማራ በሚባለው አካባቢ የወያኔ ባለስልጣኖች ሰፋ ያለ ሹም ሽር ለማካሄድ የተዘጋጁ መሆናቸውን ለማወቅ ትችሏል። አጠቃላይ በሆነ ደረጃ ወያኔዎች ተቅሊጥ በማለት የሚጠሩት ፕወዛ እንደሚደረግ ከውስጥ አዋዊዎች የተገኘው መረጃ ያስረዳል፡፡ ባለፈው በኦሮሞው አካባቢ የሕዝብ አመጽ በተካረረበት ወቅት ሕዝብንና በሙስና ዝርፊያ ያካሄዱና ለአባዱላና ለመሰሎቹ የገንዘብ ምንጭ በመሆን በተለያዩ ከተሞች ገዢ የነበሩትን እያሰሩ ወህኒ ማውረዳቸው የሚታወቅ ሲሆን በተመሳሳይም መንገድም የነበረከት ስምዖን የገንዘብ ምንጭ የሆኑ በርካታ የአማራ ሹሞችን እየቀፈደዱ ዘብጥያ እንዲወርዱ የስም ዝርዝር ለቀማው መጠናቀቁ እየተሰማ መሆኑም በሰፊው ይነገራል፡፡
ወያኔ በኮንሶ ሕዝብ ላይ እያካሄደ ያለው ጭፍጨፋ አሁንም ያልቆመ መሆኑ ተገለጸ። በትናንትናው ዕለት የወያኔ የጸጥታ ኅያሎች ባካሄዱት የቤት ለቤት አሰሳ ባካሄዱት ጥቃት አንድ ሰው ሲገደል 3 ስዎች ለከፍተኛ የአካል ጉዳት ተዳርገዋል። በተጨማሪም ከስድሳ በላይ የሚሆኑ ዜጎች ከቤታቸው እየተለቀሙ ተወስደው ታስረዋል። ባሳልፈነው ሳምንት ብቻ ከአካባቢው ከ25 በላይ የሚሆኑ ዜጎች የተገደሉ ሲሆን ከ12 ሺ በላይ የሚሆኑ ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው ለስደት ተዳርገዋል ተብሏል።
ሰኞ መስከረም 9 ቀን 2009 አ.ም.በአሜሪካ ዋና ከተማ በዋሽንግተን ዲሲ በ25 ዓመት ውስጥ ከታዩት ላቅ ያለ ትዕየንተ ህዝብ ተካሂዷል። ከተለያዩ ከ 20 በላይ ከሆኑ የአሜሪካ ግዛቶች በትላልቅ አውቶቡሶችና በተለያዩ መጓጓዣ በመጠቀም በርካታ ሺህ ለሀገር ለወገን የተቆረቆሩ ኢትዮጵያውያን የተገኙበት ነበር። በወያኔ አግአዚ ጦር እየተካሄደ ያለውን አረመኔያዊ ጭፍጨፋ ለመቃወም እንዲሁም ለነጻነቱ እየታገለ ያለውን ሕዝብ ለመደገፍ የወያኔ ሸሪክ የሆነችው አሜሪካንን ለመኮንን በነቂስ የወጣው ሕዝብ ከዚህ ቀደም ከታዩት በቁጥር በርካታ ሺ ሕዝብ የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ እያውለበለበ በዋሽንግተን ዲሲ ዋና ዋና ጎዳናዎችን ለአራት ሰዓታት ያህል ዘግቶት ውሏል። የአየር ሁኔታው አሸጋሪ ሆኖ በላዩ ላይ የሚዘንበትን የማያቋረጥ ዝናም ከምንም ባለመቁጠር እየፈሰሰ ካለው የወገን ደም አይብስም በማለት ለወገኑ ያለውን ተቆርቋሪነት አሳይቷል። መነሻውን ከአሜሪካ ውጭ ጉዳይ አድርጎ መድረሻውን የአሜሪካ ምክር ቤት ያደረገው ስለፈኛ የተለያዩ መፈክሮችን ከማንሳቱ ባሻገር የተለያዩ መልክቶች በተለያዩ ተናጋሪዎች ተደምጠዋል። ሰልፉን ድምቀት ከሰጡት መካከል የሃይማኖት አባቶች በርከት ብለው በመገኘት ሰላማዊ ሰልፉን መርተውታል። በአማርኛ፤ በኦሮሚኛ እንዲሁም በእንግሊዘኛ ቋንቋ ሲስተጋቡ ከነበሩት መፈክሮች ውስጥ ደማቅ የነበረው ደማቸው ደማችን ነው የሚለው ነበር።፡ዛሬ በአግአዚ መጋዝ እየተገዘገዘ ያለውን የኢትዮጵያውያንን ነፍስ በትልቁ ቁጭቱን ሀዘኑን ገልጿል። የአማራው ድም ደሜ ነው፤ የኦሮሞው ደም ደሜ ነው፤ የኮንሶ ደም ደሜ ነው፤ የአፋሩ ደም ደሜ ነው፤ የጋምቤላው ደም ደሜ ነው፤ የኦጋዴኑ ደም ደሜ ነው የሚሉት መፈክሮች ቀዳሚ ቦታ ይዘው ነበር።
ሰኞ መስከረም 9 ቀን 2009 ዓ.ም. በአሜሪካ የካሊፎርኒያ ግዛት ሎስ አንጀለስ ከተማ የሚገኘውን የወያኔን ቆንስላ በአካባቢው የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ለ 45 ደቂቃ ያህል በቁጥጥር ስር አውለውት እንደነበር ተዘግቧል። ኢትዮጵያውያኑ የወያኔ አገዛዝ ያወገዙ ሲሆን በቆንስላው ላይ ተሰቅሎ የነበረውን ባለኮከቡን የወያኔ ባንዲራ አውርደው የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ እንዲውለበለብ አድርገዋል። በወያኔ የተገደሉ ዜጎች ምስሎችም በትነዋል። እንዲሁም በትናንትናው ቀን በእስራኤል አገር የሚኖሩ ትውልደ ኢትዮጵያውያን እየሩሳሌም በሚገኘው የአሜሪካ ኢምባሲ ፊት ለፊት በመገኘት የተቃውሞ ሰልፍ አድርገዋል። ወያኔ በአገራችን ዜጎች ላይ እያካሄደ ያለውን ጭፍጨፋ በከፍተኛ ደረጃ አውግዘው የአሜሪካ መንግስት ለዚህ የገዳይ ቡድን የሚሰጠውን ርዳታ ባስቸኳይ እንዲያቆምና በአገዛዙ ላይ አስፈላጊውን ጫና እንዲያደርግ ጠይቀዋል።
#ማክሰኞ መስከረም 10 ቀን 2008 ዓም. በሱዳን የወያኔ የግብጽና የሱዳን ባለስልጣኖች ስለአባይ ግድብ ሁኔታና እንዲሁም ግድቡ በሌሎች አገሮች ላይ ስለሚያስከትለው የአካባቢውና የኢኮኖሚ ክስተተች ጥናት ከሚያጠኑ ተቋሞች ጋር የይፋ ስምምነት ያደረጉ መሆናቸው ተገለጿል። ስምምነቱ የተፈረመው አርተሊያና ቢ አር ኤል ከሚባሉ የፈረንሳይ ኩባንያዎች ጋር ሲሆን ለኩባንያዎቹ የሚከፈልውን 4.5 ሚሊዮን ዩሮ ሶስቱም አገሮች በእኩል ሊከፍሉ ቃል ገብተዋል።
ሰኞ መስከረም 9 ቀን ሶማሊያ ውስጥ አልሸባብ በወያኔ ጦር ላይ የደፈጣ ውጊያ አካሄዶ ጉዳት ያደረሰ መሆኑን ጋርዋ እየተባለ የሚጠራው ድረገጽ ዘግቧል። አልሸባብ የደፈጣ ውጊያውን ያካሄደው መሀዝ በተባለው ግዛት በሂራን አካባቢ ሲሆን ለረዥም ጊዜ የተኩስ ልውውጥ የተደረገ መሆኑ ተጠቅሷል። በውጊያው ከሁለቱም በኩል የደረሰው ጉዳት ምን እንደሆነ እስካሁን የተገኘ ዝርዝር መረጃ የለም።
ለዝርዝር ዜና:
To Read: http://www.finote.org/news.pdf
To Listen PART 1: http://www.finote.org/TodayPart1.mp3
To Listen PART 2: http://www.finote.org/TodayPart2.mp3