ዜና ፍኖተ ዴሞክራሲ (መጋቢት 16 ቀን 2008 ዓ.ም.) – የወልቃይት ጠገዴ ሕዝብ ያነሳውን የማንነትና የመብት ጥያቄ የወያኔ መሪዎች ሚሊሺውንና የፖሊስ ኃይሉን ከትግራይ በማስመጣትና ወታደሩን በማስፈር ምላሽ በመስጠት አስፈራርተውና አሸብረው የታላቋ ትግራይን ህልውና እውን ለማድረግ የጀመሩት ሙከራ አሁንም ከሕዝብ ከፍተኛ ተቃውሞ እንደገጠመውና ውጥረቱ እየከፋና ግጭቶችም እየበረከቱ መምጣታቸው ከአካባቢው የሚመጡ መረጃዎች ያመለክታሉ – በምዕራብ ወለጋ በመንዲ ከተማ አንድ የገበያ ማዕከል በእሳት አደጋ እንዲወድም ከተደረገ ወዲህ ሕዝባዊ ተቃውሞ በማገርሸቱ የወያኔ ፖሊሶች የመንዲ ከተማ ተማሪዎችንና መምህራንን አስረው ወደ አልታወቀ ሰፈራ እንደወስዷቸው ታውቋል – በመቀሌ የጀመረው የባጃጁ የሥራ ማቆም አድማ አሁንም እንደቀጠለ ሲሆን የወያኔ አገዛዝ በርካታ የታጠቁ ፖሊሶቹንና ወታደሮችን በከተማ ውስጥ በማስፈር ሕዝብን እያስፈራራና የባጃጅ ሹፌርና ባለንብረቶችንም እያዋካበ እንደሚገኝ ታውቋል – ከአስር ሚሊዮን በላይ ኢትዮጵያውያን በድርቅና በረሃብ አደጋ መጠቃታቸው እየተነገረ ባለበትና ከፍተኛ የሆነ የሰዎች ሞትና ዕልቂት እንዳይከሰት የዓለም አቀፉ ኅብረተሰብ በፊት ርብርብ በሚያደርግበት ሰዓትና በሀገር ውስጥ ያለው የእርዳታ እህል መጠን ከሁለት ወር በላይ አያራምድም በሚባልበት ጊዜ በጂቡቲ ወደብ የእርዳታ ስንዴ ማራገፊያ ማጣቱ ተገለጸ – በልዩልዮ ሰበብና ምክንያት የሕዝብ ገንዘብ መሰብሰብና መዝረፍ መለያ የሆነው ወያኔ በባለተሽከርካሪዎች ላይ ተጨማሪ የግዳጅ ገንዘብ መሰብሰቢያ ዘዴ ጀምሯል – ማኅበረ ቅዱሳን ከመጋቢት 15 ቀን እስከ መጋቢት 21 ቀን 2008 ዓም ድረስ በአዲስ አበባ ከተማ በኢግዚብሽን ማዕከል ኦርቶዶክሳዊ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያንን አስተምህሮዋን እንጠንቀቅ ድርሻችንን እንወቅ በመሪ ርዕስ ያዘጋጀውን ዐውደ ርዕዩትን በመጨረሻ ሰዓት ላይ በወያኔ ባለሥላጣናት መከልከሉ ታወቀ – በብራስልስና በፓሪስና በጀርመን ተጨማሪ አሸባሪዎች ተያዙ – በግብጽ ጣሊያናዊውን ተመራማሪ የገደሉት የተያዙ መሆናቸውን የግብጽ መንግስት አስታወቀ – በናይጄሪያ 300 የሚሆኑ የንግድ ኩባንያዎችና ግለሰቦች በሙስና ለፍርድ ይቀርባሉ ተባለ – የቀደሞ የቦዚኒያ ስርብ መሪ ተፈረደበት:: ዝርዝር ዜና ያንብቡ ወይም ያዳምጡ::