ዜናና ኃተታ (ሰኔ 10 ቀን 2009 ዓ.ም.) – የወባ በሽታ ወደ ደጋማ ቦታዎች እየተሰራጨ ነው – ከጂቡቲና ከኤርትራ ወሰን የካታር ሲነሳ ሻዕቢያ ወታደሮቹን አሰማራ – አንዳንድ የተቃዋሚ ድርጅት ነን የሚሉ በአስመራ ለማካሄድ ያቀዱት ስብሰባ ተወገዘ – በሊቢያው መአመር ጋዳፊ ላይ የተዘመተው አንድ የአፍሪካ ገንዘብ እንዲኖር እንቅስቃሴ በመደረጉ ነው ተባለ – በምስራቅ ኢትዮጵያ አንድ ጥንታዊ ከተማ በተመራማሪ ቡድን ተገኝ – የኢትዮጵያ ፖለቲካ እስረኞች አንድነት ኮሚቴ በወያኔ ታፍነው ስለሚሰቃዩ እስረኞች የሚደረገው እንቅስቃሴ ደካማነት ተቸ።
ባለው የአካባቢ ደህንነት መበላሸት የተነሳ የወባ በሽታ ወደ ተራርማ ቦታዎችና ወደ ደጋውም እያቀና ነው የሚል ዜና ተሰራጭቷል። ወያኔ ደን መጨፍጨፍና ማስጨፍጨፍ ልማዱ ነውና የአየር ጠባይ መዛባት ለወባ መሰራጨትና መስፋፋት ምክንያት መሆኑም ተረጋግጧል። ባለው ሁኔታ የወባ በሽታ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎችን እንደሚያጠቃና ወያኔ ደግሞ ከክልል አንድ ውጪ ወባን ለመከላከልና ለማጥፋት የሚያደርገው ጥረት ዝቅተኛ መሆኑም ተጋልጧል ። በጤና ጥበቃው መስክ የወያኔው ባለስልጣን ቴድሮስ አድሃኖም በዘረኛ ፖለቲካ ተመርቶ ያደርገው እንቅስቃሴና የደረሰውም ጉዳት የሚረሳ አይደለምና ይህን ዘረኛ ግለሰብ የማጋለጡና የመቃወሙ እንቅስቃሴ በዓለም አቀፍ ደረጃ እንዲስፋፋም ማሳሰቢያ ተሰጥቷል።
በመካከለኛ ምስራቅ በካታር ላይ ሳውዲ አረቢያና የአረብ ባህረ ሰላጤ የከፈቱት ዘመቻ ባስነሳው ቀውስ መሰረት ሻዕቢያ በሳውዲ ጎን በመስለፉ ምክንያት በጅቡቲና ሻዕቢያ መሀል በነበረው የድንበር መሬት ግጭት በዱሜራ ተራራ ሰፍሮ የነበረው የካታት ጦር ጠቅልሎ በመውጣቱ ሻዕቢያ ሳይውል ሳያድር ሶስት ባታሊዮኖችን ልኮ የውዝግቡን መሬት መያዙን አስታውቃ ጅቡቲ ክስ አቅርባለች ። ሻዕቢያ ለስልጣን እንደበቃ ከጎረቤት አገሮች በሞላ በድንበር ጉዳይ ውጊያ የገጠመ መሆኑ መታወስ አለበት ያሉ ክፍሎች በግርግርም ዱሜራ ተራራን ገቢ ሊያደርግ ተቀላጥፏል ሲሉ ከሰዋል። ይህ በዚህ እንዳለ ላለፉት በርካታ ዓመታት ሻዕቢያ የጅቡቲን የአፋር ተቃዋሚ ሀይል–ፍሩድ የሚባለውን– በትጥቅና ስልጠና ሲረዳ መቆየቱም የሚታወቅ ነው ። ለአል ሸባብም፤ ለወያኔ ተቃዋሚዎችም ወዘተ ምንም አልረዳሁም ብሎ መካድ ልምዱ የሆነው ሻዕቢያ በጅቡቲ በሀገራዊ ጉዳይ ጣልቃ ገብቶ መገኘቱ የሚታወቅ ነው ተብሏል ። ሻዕቢያ ፍሩድን ቢረዳም አፋር በመሆናቸው ወደ ኢትዮጵያ የሚያዘነብሉ አፋሮች እንዳይጠናከሩ በጎን ደግሞ ሻጥሩን እየፈጸምባቸው መሆኑን ውስጠ አዋቂዎች ያጋልጣሉ። የኢትዮጵያ ተቃዋሚ ሀይሎችን እረዳለሁ እያለ ሻዕቢያ እንዳሽመደመዳቸው የጠቀሱ ታዛቢዎች ከሻዕቢያ ተጠግቶ ስርየት ፍለጋ ከንቱ ነው ብለዋል።
በምስራቅ ኢትዮጵያ ሀርላ ውስጥ ዕድሜው ከከረሰቶስ ለደት በዃላ 10ኛው ምዕተ-ዓመት የሚሄድ ጥንታዊ ከተማ የታሪክ ተመራማሪ ቡድን ማግኘቱ ታወቀ። ምነጫቸው ከግብጽ፣ ከህንድና ከቻይና የሆኑ ቀርሳ ቅርሶች አብረው መገኝታቸው አካባቢው ከፍተኛ የንግድ ለውውጥ ይደረግበት አንደነበረ ያሳያል ተብሏል። ከዚህ በተጭማሪ በ12ኛው ምዕተ ዓመት የተሰራ፣ ታንዛኒያና ሶማሊላንድ ከተገኙት የሚመሳሰል መስጊድም መገኘቱንና ቡድኑ በዚሁ አካባቢ በተገኘ መቃበር ቁፈራው 300 የሚሆኑ የሰው አጽሞች ማግኝቱንና ይመገቡ የነበረውን የመገብ አይነትም ለማወቅ ምርመራ ላይ መሆኑን አያይዞ መግለጡን ከዓለም ዓቀፍ የዜና ምንጮች ዘገባ ማወቅ ተችሏል።
የኢትዮጵያ ተቃዋሚ ሀይሎችን ነን የሚሉ አንዳንድ ቡድኖች ህብረት መስረታን በተመለከተ በሻዕቢያ አጋፋሪነት በአስመራ ስብሰብ ለማድረግ እየተዘጋጁ ነው የተባለው ዜና ከልዩ ልዩ አቅጣጫ መወገዙ ተዘግቧል። በሻዕቢያ የበላይ ተቆጣጣሪነት ለኢትዮጵያ የሚበጅ ምንም ህብረት ወይም ጥረት ሊኖር እንዳማይችል ያለፉት 26 ዓመታት በግልጽና በምሬት በደምም አሳይተውናል ያሉ ክፍሎች የኢትዮጵያ ዕጣ ፈንታ በኢትዮጵያውያን እጅ እንጂ በሻዕቢያ መዳፍ ወይም ጫማ ስር አይገኝም በሚል ምሬታችውን ከወዲሁ ገልጸዋል ። በዚህ ጎጂ ዕቅድም መሰማራትን በአስቸኳይ እንዲያቆሙም አሳስበዋል።
የሊቢያውን ሞአመር ጋዳፊ የአውሮፓው የጦር ስብስብ ኔቶ የዘመተበት ለሊቢያ ሕዝብ ነጻነት ሳይሆን የሊቢያን ቤንዚን/ዘይት ሀብት ለመቆጣጠርና ጋዳፊ አንድ የአፍሪካ ገንዘብ–ከዩሮም ከዶላርም ያልተቆራኘ–ይኑር ብሎ የጀመረውን እንቅስቃሴ በአጭር ለመቅጨት መሆኑ በሂላሪ ክሊነትን ምስጢራዊ የኢ ሜይል ደብዳቤዎች ተጋለጠ። ለፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ሳርኮዚ ምርጫም ጋዳፊ 50 ሚሊዮን ዩሮ ረድቶ ስለነበር ይህም በቃሉ እንዳይጋለጥ የጋዳፊን መገደል ፈረንሳይ አጥብቃ መግፋቷ ተጋልጧል። የአፍሪካ ንብረት ለአፍሪካውያን የሚለውን መፈክር ገቢራዊ ለማድረግ የገፉ የአፍሪካ መሪዎች ሁሉ (ንክሩማህ፤ ሉሙምባ፤ ካብራል፤ ማሼል፤ ወዘተ) ሁሉም ለጥቃትና ለሞት መዳረጋቸው ያትወቃል ያሉ ታሪክ አቅዋቂዎች የጋዳፊም መጠቃትና መገደል ለአፍሪካ ነጻነት ከነበረው አቅዋም ጋር የተያያዘ ነው ብለዋል። ኢትዮጵያን በተመለከተ ጋዳፊ የኢትዮጵያ ጠላት ወያኔና ሻዕቢያን ደጋፊ እንደነበር ግን መቸም የሚረሳ አይደለም ሲሉ ታዛቢዎች ተችተዋል።
በወያኔ ተይዘው ደብዛቸው ስለጠፋው እና በህገወጥ መንገድ ተይዘው አለፍርድ ስለታገቱት የሚደረገው እንቅስቃሴና ተቃውሞ ደካማ ነው ሲል የኢትዮጵያ የፖለቲካ እስረኞች አንድነት ኮሚቴ በሰሞኑ ተቸ። እነ አበራሽ በርታ፤ ለማ መኮንን፤ ተስፋዬ ከበደ፤ ወንዱ ሲራክ ደስታ፤ ወዘተ ከጠፉ ከሀያ ዓመት በላይ ያለፈ ሲሁን ተጠልፈው ለእስር የተዳረጉትና ፍትህ የተነፈጉት እነ አንዳርጋቸው ጽጌም ቢሆን የሚደረግላቸው ዘመቻ እየደከመ እንጂ እየተጠናከረ አልሄደም ተብሏል፡፤ በአንጻሩ በጎንደር የፖለቲካ እስረኞችን አስፈታን እየተባለ የሚነገረው ከሀቅ ጋር ያልተገናነ ነው ያለው ኮሚቴው የፖለቲካ እረኞች ይፈቱ ዘመቻው መጧጧፍ ሲገባው አስፈታናቸው ውሸትን ማሰራጨቱ ጠቀሜታው ለወያኔ ብቻ ነው ሲል ደምድሟል።